የመስቀሉ ፍቅር ይገርማል

230

የመስቀሉ ፍቅር ይገርማል
የመስቀሉ ፍቅር ይደንቃል
ሚስጥር ነው እሱስ ሚስጥር ነው /2/
የምናዳምጠው የምናስተውለው
ጌታ ሚስጥር ነው በመስቀሉ የሰራው

አንድ በሎ ሲጀምር ጉዞውን
ጌታ ተቀበለ እርግማኔን
ጨርቁን ቀደው ተካፈሉት
እንዲፈጸም ነቢያት የጻፉት

በመስቀል ላይ ጌታችን ተሰቀሏል

እጆቹንም ችንካሩ ይዞታል
ከጎኑ ውሃ እና ደምም ፈሳል
የሾህ አክሊል በራሱ ተደፍቷል
በዛውስጥም እንኳን ፍቅሩ ይታያል

ብልህ ሆኖ ጌታ ተታለለ
ምንጭ ሳለ ተጠማሁኝ ኣለ
ኮምጣጤ አምጠተው አጠጡት
አይሁድ እያፌዙበት

ኦ ፍቅሩ አስገራሚ ምህረቱ አስደናቂ
ትእግስቱ አስገራሚ ነው ውለታው እጅግ በዙ ነው

እውነት ነው የመስቀሉ ፍቅር
እምነት ነው የመስቀሉ ፍቅር
ሚስጥር ነው በመስቀሉ ጌታ ምናየው
እንምበርከክና እና እንረዳው /4/

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top