መድኃኒታችን ተወልዷል

4

የዓለም ፈጣሪ ታላቁ ጌታ
ሁሉ በእርሱ የሆነ የማይረታ /2/
መድኃኒት ተወልዷል ዛሬ በበረት
ስሙን እናመስግን እንዘምርለት /2/
አሜን እንዘምርለት

ቃል እንደ ነበረ መቼ ቀረና
በመንፈስም ሰርጾ ተወልዷልና /2/
ዝማሬአችንንም ለእርሱ እናዜማለን
በሰማይ በምድር ሰላም ይሁን ብለን /2/
ኢየሱስ ሰላምን ስጠን

መድኃኒታችን ተወልዷል
ክብሩንም በዓይናችን አይተናል
ክብርም ለእርሱ ይሁንለት
ወድቀን ከፊቱ እንስገድለት

የሰላሙ መሪ መጥቷል ወደኛ
ሊያድነንም ፈቅዶ በበረት ተኛ /2/
ፍቅሩ የማይሻር ዘለዓማዊ ነው
ሁሌም ዘወትር ክበር እንበለው /2/
ዛሬም ክበር እንበለው

ክብሩ ሞገሱ ከሁሉ ይበልጣል
እርኩስ መንፈስ ያንቀጠቅጣል2/

እውር ሽባውም በስሙ ይድናል
መድኃኒት ሆኖ ሁሉን ይፈውሳል2/ ኢየሱስ ተወልዷልና

የልደት

Leave a Comment

Scroll to Top