ዋስትና የለኝ እኔ
ስኖር በዘመኔ
የሚያስተማምነኝ
አንዳች ነገር የለኝ
በምደር ላይ ስኖር እኔ በዚች ዓለም
የሚያኮራኝ ለኔ አንዳች ነገር የለም
ዘመኔን ላበርክት ያንተ ሆኜ እኔ
ላገልግልህ አንተን ስጠኝና ወኔ
እስከዘላለሜ ያንተ ህይወት እንዳገኝ
በፀጋህ ባርከኝ በረከትም ስጠኝ
አላማዬ ይሁን እኔ አንተን ማመኔ
እራሴን ልሰዋ ሙሉውን ዘመኔ
በምድር ላይ ሳለሁ በጣም መልካም ወዳጅ
ዘመድ ሁነኝ አንተ ከሁሉም የሚበጅ
ስጦታህን ስጠኝ እንዳገለግልህ
ተመስገን ተወደስ ዘወትር እንድልህ
