በፍቅር ወዶኛል

-

1. ለጻድቅ ሰው የሚሞት ድንገት ይገኛል
ለነፍሱም ሳይሳሳ ቢሰጥም ያምራል
መሞቴን ሊሞትልኝ ኢየሱስ ወደደ
ለኃጢአተኛው እኔ ስለኔ ታረደ

አላስቀምጥ አለኝ ሳስብ ይኼን ፍቅር
ምንኛ ብርቱ ነው ውስጥን የሚነዝር
የመስቀል ላይ ጣሩ ሁሉም ይታየኛል
በእውነት ልዩ ነው በፍቅር ወዶኛል

2. አቅም ብርታቱን አጥቶ ሲወድቅ ሲነሳ
አላዋቂ ሰው መስሎ እኔ የተነሳ
በነፍሱ ላይ ቆረጠ ሊያኖር የኔን ነፍስ
አፈቀረኝ ኢየሱስ እስከ ሞት ድረስ

አላስቀምጥ አለኝ ሳስብ ይኼን ፍቅር
ምንኛ ብርቱ ነው ውስጥን የሚነዝር
የመስቀል ላይ ጣሩ ሁሉም ይታየኛል
በእውነት ልዩ ነው በፍቅር ወዶኛል

3. አንዱንም ሳይገባኝ ኢየሱሴ ካረገው
በመስዋትነቱ ሁሉንም አገኝሁ
ቀስቃሼ ሆኖልኛል ለኔስ ይኼ ምስጢር
አላስቀምጥ የሚል ውስጥን የሚነዝር

አላስቀምጥ አለኝ ሳስብ ይኼን ፍቅር
ምንኛ ብርቱ ነው ውስጥን የሚነዝር
የመስቀል ላይ ጣሩ ሁሉም ይታየኛል
በእውነት ልዩ ነው በፍቅር ወዶኛል

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top