አምንሃለሁ

126

ጌታ ቃልህን እጅግ አውቀዋለሁ
ፅድቅህ የዘለአለም ስንቅ ነው
ትዕዛዝህም ለኔ ተድላዬ ነው
ምስክርህ እኔ ሁሌም አምንሐለሁ
በሕይወቴ ስላየሁ አምንሃለሁ

ህግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴም ደግሞ ብርሐን ነው
እመራበትም ዘንድ ጌታ እኔማ እምላለሁ
ነፈሴ ሁልጊዜም በእጅህ ውስጥ ናት ጌታ ኣስባት
ተሰናክላ እንዳትወቅ አንተው ብርታት ሁናት

እንደቸርነትህ አቤት ድምፄን ስማ አባቴ ሆይ
ወደአንተ ወስድህ አድነኝ ደርሰህ ከዚያ ስቃይ
የከበደኝ ሸክም ለአንተ ይቀልሐል ጌታ ይቻልሐል
ከላዬ አራግፈው ሁሉ ይታዘዝሐል ምን ይሳንሐል

አይኔ ሳያማትር በአንተ ላይ ይረፍ
ሐሳቤም ይረፍ
እንደ ሐዋሪያት መጠሪያዬ ይሁን አንተን ማመን
ዋጋዬ በሰማይ እጅግ ይበዛና
ባርኮቱ ያይልና
የዛሬን መከፋት ያኔ እረሳለሁ
እንባዬንም በአንተ አብሳለሁ
አምንሐለሁ /3/ ጌታዩ እታመንብሐለሁ
አውቅሐለሁ /3/ አባቴ እመሰክራለሁ
እጠራሐለሁ /3/ ኢየሱስ እጠብቅሐለሁ

በጉብዝናዬ ወቅት ጉልበቴ በበረታበት
አቅሜ በበዛበት
ለአንተ እራሴን ላቅርብ ለማገልገል
ሳልቆጥብ ከመስጠት
ኋላ እንዳይቆጨኝ ይህ ጊዜ ያልፍና
ሁሉ ይቀየርና
ፀፀቱ ሐያል ነው ሚስጥሩ ሲገባኝ
እውነቱ ሲታወሰኝ
አምንሃለሁ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top