እሻገራለው /2/
ዮርዳኖስ ሞልቶ ከፊቴ ባየው
ጠላቴም ደርሶ ልቤን ቢያርደው
እሻገራለው
አመልከዋለው /2/
እንደማይተወኝ ይህን አውቃለው
ጌታን የያዘ ሁሌ ድል ኣለው
አመልከዋለው
ጀግና መስዬ በጠላቴ ፊት
ስፎክር ብውል አላሸነፍኩት
ግን እግዚአብሔር አግዘኝ ስለው
ስራዬን ሰራ ጠላቴን ጣለው
ብዙ ብዙ ምስጋና ላንተ
ብዙ ብዙ ዝማሬ ላንተ
ብዙ ምስጋና
ተመስገን ብዬ ጌታ ሳከብርህ
ክብሩን ውሰደው እኔንም ባርከህ
አንተ ስትረዳኝ እበረታለው
እጄን ተይዤ እሻገራለው
ብዙ ብዙ ምስጋና ላንተ
ብዙ ብዙ ዝማሬ ላንተ
ብዙ ምስጋና
