አቁመኝ በአላማዬ

34

አቁመኝ በአላማዬ አቁመኝ
ኣቁመኝ በአላማዬ አቁመኝ
አቁመኝ ያለነቀፋ እንዳገለግልህ
ፀጋህን አብዛልኝ /2/

የአንተ አላማ በእኔ
ይከናወን ዘንድ በመፍቀድህ
ከአለም ጠራኸኝ መረጥከኝ
ለወጥከኝ አቆምክኝ በቤትህ
እኔም በመሰጠት ለክብርህ
ለማገልገል አንተን በትጋት
ዓላማዬ ይህ ነው ጌታዬ
ፀጋህን አብዛልኝ እለት እለት

ዓላማዬ አንተ ነህ እግ/ር
መኖር ለክብርህ በዘመኔ
አንተን ማገልገል ነው መሻቴ
ስለዚህ አትለይ ከጐኔ
የአንተን ተግባር ይግለፅ ተግባሬ
አሳቤ አንደበቴ ህይወቴ
በአላማዬ አቁመኝ ሁልጊዜ
ፀጋህን አብዛልኝ አባቴ

በዚህ በመጨሻው ዘመን

ሰው አምላኩን በዘነጋበት
ያንተን ስራ ሰርቼ ልለፍ
ቁም ነገርን ሳለሁ በህይወት
ቅድስናህ ይታይ በህይወቴ
በሃሳቤ ተግባሬ አንደበቴ
ዓላማዬ ይህ ነው ጌታዬ
ፀጋህን አብዛልኝ አባቴ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top