አንተን ማመስገን ስራዬ ይሁንልኝ ለኔ
ዕለት ዕለት ደግነትህን እያየሁ ባይኔ
ይህንን ልመስክር በዘመኔ
ህይወትን አቅደህ የሰጠኸኝ ዕለት
ከመጀመሪያዋ እስከአሁኗ ሰዓት
መባረኪያ መንገድ አድርገህ ብትይዛት
እንዳትሆን ለሁሉም በአድናቆት የሚያዩአት
ሆነችልኝ ለኔ የማመስገን ምክንያት
ትኩረትን ሰጥተኸኝ ስትሰማ ጩኸቴን
ገና በሩቅ ሳለሁ ተረድተህ ምኞቴን
ካህናት ያዩኝ ዘንድ እንድሄድ ስታዘኝ
እሺ ብዬ ስሄድ ኃይልህ መንፃት ሆነኝ
ውስጤም ተነሳሳ ሂድ አመስግን አለኝ
አለማመስገኔ ነውረኛ የሚያሰኘኝ
ያልተደረገልኝ ውለታ ቢስ የሚለኝ
አንተን ማመስገን ስራዬ…..
ከአንተ እንደሆንኩ እንዳውቅ መነሻዬ
ኖረህ የምታኖረኝ ዘወትር አለኝታዬ
በማመን የምትረዳኝ አንድ አንተ ነህ ብዬ
በድፍረት የምናገር መልዕክተኛ ሆኜ
ማመስገን ግድ አለኝ አንተን ፈጣሪዬ
ሳነብ ታሪኮቼን ጣቶችህ የፃፏቸው
ድንቅ ስራችህን ጠንቅቄ የማውቃቸው
አንተን ማመስገን ስራዬ…..
ለካ ብዙ ናቸው ልቤ የማይረሳቸው
በምስጋና አንደበት ሁሌ የማነሳቸው
በውዳሴ ዜማ ልቤ የሚያዜማቸው
አንተን ማመስገን ስራዬ….
