ከብርሃናት በፊት አለህ በመንግስትህ የምትኖር
በሥልጣንህ የማትፈጠር መጀመሪያ ፍፃሜ የሌለህ
መልክና አምሳያ መለያችን ይሁን ብለህ
ለክብርህ አበቃኸን እስትንፋስን ሰጥተህ
ትኖራለህ ይሁን ትላለህ ታፀናለህ ታስተዳድራለህ
የፍጥረታት ጌታ የሕይወት ባለቤት
ሁሉም ላንተ የሆነ ዓይንህ ያረፈበት
ዘመን የማይቆጥርህ ጊዜ የማይገድብህ
የዘለዓለም አምላክ አንተ ብቻ ነህ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይናገራሉ ያሰለጥናሉ
ያስጨንቃሉ ይመክራሉ ያከብራሉ
በድንቅ ባህሪያቸው የሚሰሩ በሁሉ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይፈፅማሉ
ያጠራሉ ይጋርዳሉ ያስማማሉ ያከናውናሉ
እግዚአብሔር ስትሰራ ረቂቅ ነው መንገድህ
ያላሰብከው የለም ያልዳሰስከው በእጅህ
ልቦናው ነቅቶለት ለተገነዘበህ
ዘመኑን ባርከህ ታሰምርለታለህ
