አዝ፦ አንተ ምሥጋናዬ ነህ /3/ ለዓመታት
አንተ ምሥጋናዬ ነህ /3/ ለዘመናት
1. ክፉ ሲመጣ ያመለጥኩብህ
ስጣል ስረሳ የታቀፍኩብህ
በአንተ እዚህ ደረስኩ ከእኔ ጋር ሆነህ
ኢየሱስ ለእኔ ምስጋናዬ ነህ
አዝ፦ አንተ ምሥጋናዬ ነህ /3/ ለዓመታት
አንተ ምሥጋናዬ ነህ /3/ ለዘመናት
2. አይኔ አየችህ አትደክምም በእኔ
ባልመችህም ሰው በመሆኔ
ምሥጋናን ላውጅ በቤትህ ዙሪያ
ነፍሴ ትባርክህ ቆማ እንደገና
አዝ፦ አንተ ምሥጋናዬ ነህ /3/ ለዓመታት
አንተ ምሥጋናዬ ነህ /3/ ለዘመናት
3. በጠላቴ ፊት ሞገስ ሆንክልኝ
በእሳት መካከል አደላደልከኝ
በአንተ ተደገፍኩ ምርኩዝ ሆንክልኝ
አሜን ኢየሱስ ተባረክልኝ
አዝ፦ አንተ ምሥጋናዬ ነህ /3/ ለዓመታት
አንተ ምሥጋናዬ ነህ /3/ ለዘመናት
4. በድካም ጐኔ አንተ ቆምክልኝ
ጠላቴን ታግለህ አሸነፍክልኝ
የት ያገኘኛል ተሻግሬአለሁ
ከአንተ የተነሳ በአብ ቀኝ አለሁ
አዝ፦ አንተ ምሥጋናዬ ነህ /3/ ለዓመታት
አንተ ምሥጋናዬ ነህ /3/ ለዘመናት
