1. ፍቅርህ ታላቅ ነው ለእኛ ብዙ ውለሀል
እሩሩነትህ ብዙ ነው ምህረት ሞልቶሀል
እንዳንተ ያለ አባት ጌታ ሆይ ከቶ አናገኝም
ፍቅርህ ማርኮናል ጠርቶናል አንሄድም የትም
እናሸበሽባለን ላንተ/4/
2. የአባትነት ፍቅርህን አልነፈከንም
ብንከፋም ግርማ ሞገስህ አላሸሸንም
ብንርቅም ፍቅርህ አባብሎ ከአለም ጠርቶናል
እንወድሀለን ሁሌ ባንተ ደስ ይለናል
አናጨበጭባለን/4/
3. እኛን ልጆህን በደምህ ዋጅተህ ያዳንከን
ባንተ ስንኖር ምን አጣን ምን ጎደለብን
ያንተ የሆነው የእኛ ነው እጅግ ታላቅ ነው
የልዑል ልጆች ተብለን እንጠራለን
አንሰግድልሀለን ላንተ/4/
4. ዛሬስ ጠላት መቼ ቆመ መቼ አረፈና
ምንም ቢዋጋ እንዳይደርስ ላንተ ምስጋና
መች አስችሎን ዝም እንላለን ውዱ አባባ
ይድረስ ጸባኦት ምስጋናችን መቅደስህ ይግባ
እናሸበሽባለን ላንተ/4/
እናጨበጭባለን ላንተ/4/
እንሰግድልሀለን ላንተ/4/
