ይበልሽ ደስ

205

ይበልሽ ደስ ነሽ ታሪካዊት
አምላክ ወደደ አንቺን ለእናት
አምላክ መረጠሽ ምን ተስኖት
ይበልሽ ደስ ነሽ ታሪካዊት
ማርያም መረጠሽ ኢየሱስ ለእናት
ለእራሱ አደረገሽ ለእርሱ መምጣት

1. ለልበ ቅኖች የልብ ነው
እግ/ር መርጦ ስህተት የለው
ማርያም በፊቱ ደስ ይበልሽ
ኢየሱስ ሞገስ ከሆነልሽ
ማርያም በፊቱ ደስ ይበልሽ
የፊቱን ሞገስ ካበራልሽ

ይበልሽ ደስ ነሽ ታሪካዊት
አምላክ ወደደ አንቺን ለእናት
አምላክ መረጠሽ ምን ተስኖት
ይበልሽ ደስ ነሽ ታሪካዊት
ማርያም መረጠሽ ኢየሱስ ለእናት
ለእራሱ አደረገሽ ለእርሱ መምጣት

2. በሁሉ ሳለ ሞልቶ ምርጫው
ለምህረት እጁ ሆንሽው መምጫው
በአለም ተሰማ ታሪክሽ
እግ/ር እንዳከበረሽ
ማርያም ብፅእት መሆንሽ /2/

ይበልሽ ደስ ነሽ ታሪካዊት
አምላክ ወደደ አንቺን ለእናት
አምላክ መረጠሽ ምን ተስኖት
ይበልሽ ደስ ነሽ ታሪካዊት
ማርያም መረጠሽ ኢየሱስ ለእናት
ለእራሱ አደረገሽ ለእርሱ መምጣት

3. ኸረ እንዴት ማርያም ጌታ አደለሽ
በፅድቁ መንገድ ላይ ተገኘሽ
የክብር ንግስት አድርጐሻል
የሰማይ አክሊል አልብሶሻል
የክብሩ ንግስት አድርጐሻል
የሰማይ አክሊል አልብሶሻል

ይበልሽ ደስ ነሽ ታሪካዊት
አምላክ ወደደ አንቺን ለእናት
አምላክ መረጠሽ ምን ተስኖት
ይበልሽ ደስ ነሽ ታሪካዊት
ማርያም መረጠሽ ኢየሱስ ለእናት
ለእራሱ አደረገሽ ለእርሱ መምጣት

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top