ኢየሱስ ሆይ ሲጠሩህ

155

ኢየሱስ ሆይ ሲጠሩህ
ደስታ ነህ ሲያሰቡህ
ከማር ይልቅ ቢያበዙህ
ላፍ ይጥማል ትዝታህ

ካንተ ወዲያ ኢየሱስ
ምን ደግ አለ ምን ልስልስ

አይሰማም ከአንተ ይብስ
ባሳብም የለ ጭርስ

ለበደሉ ተስፋ ነህ
ውብ ነህ ለሚመጡብህ
ምንኛ ቸር ነህ ለሚሹህ
ምን ትመስል ላገኘህ

ኢየሱስ ሆይ ደስታችን
ኋላም ደግሞ ገንዘባችን
በአንተ ይሁን ክብረታችን
ሐሳባችን ምኞታችን

የምትደነቅ ንጉስ
አሸናፊው ኢየሱስ
ይቸግራል በምላስ
ሲናገሩት ፍቅርህስ

ደስታ ነህ ለልባችን
ፍፁም ብርሐን ለእውቀታችን
ካንተ ወዲያ አምላካችን
ተከተተ ምኞታችን

አፋችን አንተን ይጠራል
ምግባራችን አንተን ይላል
ልባችን አንተን ይወዳል
ካንተ ወዲያ ምን ይመኛል

ኢየሱስ የሰማይ ክብር
ስትሰማ የምታምር
ለአፋችን ወለላ ማር

ለልባችንም ስኳር

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top