የፍቅሩ ምስጢር

155

እኔን ያለነቀፋ ቅዱስ ሊያደርገኝ
ጠላት የነበርኩትን በቤቱ ሊያኖረኝ
ደምና ስጋውን ከፍሎ ቢያስታርቀኝ

እኔ ተደላድዬ ቃልን ሰማሁኝ
እኔ ተመቻችቼ ነፃ ወጣሁኝ

ጥልን ሊያፈርስ ቢመጣ ክብሩን ቢያዋርድ
እኔን ሊያድን ቤዛ ቢሆን ሞትንም ቢወድ
እኔ ተማረኩ በፍቅሩ ሚስጥር
የኢየሱስ ህይወት ሆኖልኝ ፍቅር /2/
ፊተኛ ኢየሱስ ፊተኛ
መንገድ ኢየሱስ መንገድ
ህይወት ኢየሱስ ህይወት
እውነት ኢየሱስ እውነት

ሁሉ በርሱ የሆነ ኤልሻዳይ ፃድቅ
መንፈስ ቅዱስን ልኮ እኔን ሲያጠምቅ
ለኃጢያት በደሌ ስርየት ቢሆንልኝ
ሸክሜን ከላዬ ወስዶ ኣዲስ ኣረገኝ
ተቀየረ ታሪኬ ዳግም ወለደኝ

በዘላለማዊ ፍቅሩ ያደረገኝ ምርኮ
ደሙን የከፈለልኝ ልጁ ነኝ እኮ /2/
አጥቦ ለፈለገኝ ወደፍቅሩ መንግስት
ይዤ እገባለሁኝ የምስጋናን መልስ
ሁሌ እዘምራለሁ ለክብር ንጉስ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top