ኢየሱስ አትርሳን
ለቅሷችንን አድምጠን
ከጥፋት አድነን
ና ድረስልን
ገስግሰህ ድረስልን
በመከራ ጊዜያችን
እንዳንሞት ኣድነን
አንተ ነህ ጥጋችን
ስማልን ልቅሷችንን
ከጥፋት ሰውረን ናድረስልን
መሐሪ አምላክ ታደገን
በንስሐ ጎስቁለን
ካንተ በቀር ተስፋ አጣን
ዲያቢሎስ ሊፈጀን
ገሠገሠ ሊያጠፋን
አይተህ ጭንቃችንን ና ድረስልን
ምስጉን አምላክ ባይናችን
አንተን ማየት ተመኘን
ድረስ ቶሎ ቅረበን
ዘመኑ በዛብን
ዘገየብን መምጫህ ቀን
አስበን ወገንኽን ና ድረስልን
አምላካችን በፍርድ ቀን
ምርኮችህን ደስ አሰኘን
በቀኝህም አስቀምጠን
ጠብቀን ትዕዛዝህን
እንዳይጠፋ ዋጋችን
በምንሞትበት ቀን ና ደረስልን
ባለም ያሉ ፍጡራን
ያላወቁ መምጣትህን
እንዳይቀሩ በሐዘን
አትናቅ ሥራህን
አብራላቸው ብርሃንህን
አንድ መንጋ እንድሆን ናድረስልን
