እየሩሣሌም እንገባለን
ቅጥሯን በቅጡ እንሰራለን
ሆሳዕና ብለን እንዘምራለን
ዘንባባ ይዘን እልል እያልን
እየሩሣሌም አሜን /4/
ክርስትያኖች ሁሉ ኢየሱስን ያልን
በአንድነት አብረን በፍቅርም ሆነን
እንቀበል ጌታን እልፍኝ አሰናድተን
የእየሩሳለምን ቤቷን አጋጊጠን
አናዚም እንጩህ መንፈስን ተሞልተን
ለዳዊት ልጅ ክብር ሆሳዕና እያልን
እስራኤል በሙሉ ዉጡ አደባባይ
የንጉሱን ሥራ ክብሩንም እንድናይ
ስለጌትነቱ ልብስንም እናንጥፍ
ሆሳዕና ሆሳዕና ዘንባባ እንዘንጥፍ
በዙፋኑላይ ነው ከፍ ከፍ እናድርገው
ክርስቶስ ኢየሱስ ዛሬ እንግዳችን ነው
ምድርም ትታወክ ውሆዎች ይናወጡ
ለሠራዊት ጌታ እጅግ ይንቀጥቀጡ
የየሩሳሌምን ዙሪያዋን ክበቧት
የልዑል ማደሪያ ቅዱስ ስፍራችን ናት
