እላይኛው ሰማይ

190

እላይኛው ሰማይ
ሄጄ ማርያምን ልይ/2/

ሄጄ ማርያምን ልይ
ወደ ሐገሬ ገነት
እላይኛው ሰማይ
እናት እርሷ ናት

እርሷ እናቴ ናት
ተስፋዬም እርሷ ናት
ደግሞም መድሐኒት ናት
ለዚህ አለም ህይወት

እርሷ እናቴ ናት
የሁላችን ንግስት
ልሂድ ወደ እርሷ ፊት
ፍቅሬን ለማሳየት

እርሷ እናቴ ናት
አሽከሯ ለመሆን
ላዚም ምስጋናዋን
ልምሰል መልአክትን

እርሷ እናቴ ናት
መሄድ እወዳለሁ
መንበሯን አያለሁ
እኔም አከብራለሁ

እርሷ እናቴ ናት
እተዋለሁ ምድርን
እጠጋለሁ አንቺን
እንዳገኝ ፍቅርሽን

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top