በአንተ አምሳል ፈጥረኸኝ
ውብ ልጅህም አደረከኝ
አባባ እንዳይበርደኝ አንሳኝና እቀፈኝ
በጥበቃህም ስር በፍቅር አሳድገኝ
በአረሙ ተውኝ እንዳልቀር በቡቃያ
እስከ ሽምግልናዬ ሸሽገኝ በአንተ ጉያ
እንደ ሳምሶን ሀይል ሰጥተኸኝ
ፀጋህንም አበዛህልኝ /2/ አዎ
ጉልበቴ ሳይደክም በዚህ በጉብዝና ወራት
አባርሬ በምይዝበት ብሮጥም በማመልጥበት
የተመኘሁትን ሁሉ እያደረግኩ
ወደ አለም ልቤ እንዳይሳብ
የጭንቀት ቀን ሳይመጣ ዛሬ ፈጣሪዬን ላስብ
እነሆ ሁለንተናዬ ለክብርህ ይሁን እሩጫዬ /3/
ያንን አስቸጋሪ መንገድ
አልፌአለሁ በአንተ ክንድ /2/
ከማህፀን ጀምሮ እስክ ሽምግልናዬ
ከፊት ከኋላዬ ሆነህ መርተኸኛል ጌታዬ
ነፍሴ ወደ አምላኳ ስጋዬ አፈር እስኪገባ
ቀሪ ዘመኔን ባርክ ላመስግንህ አባባ /2/
ተመስገን እድሜ ሰጥተኸኝ
እንደ ማቱሳለህ ባረከኝ /2/
የሚገባህን ያህል ባሮጥም
አንተ እረድተኸኝ ግብን መታሁ /2/
በሰጠኸኝ ፀጋ መጠን ለክብርህ አስሩጠኸኛል
እነሆ ስንቱ ቀርቧል የድኳን ንሮ ያበቃል
ወደ ዘለአለማዊ ቤቴ እሄዳለው ወደ አባቴ
እኖራለሁ በሰማይ ከቅዱሳን ጋራ አብሬ /2/
ሐዘን ስቃይ በዚያ የለም
ከበጎ ጋር ጋር ለዘለአለም
ቅዱስ አግዚአብሔር እያልኩ
እኖራለሁ ለዘለአለም
