ሰዎች ያጥላሉኛል ምኑንም ሳያውቁ
መሰረቴ ህይወቴ ነው እወቁ
ተማፅኜዋለሁ የማይጠፋውን ተስፋ
መጽናት እሻለሁ ኋላ እንዳልጠፋ
እኔስ በህይወቴ ያለኝ ተስፋ ምኞት
በኢየሱስ መኖር ነው በሰማያዊው ቤት
እምነት ተስፋ ፍቅር እውነትን ጨብጬ
በአጋም እሾህ ላይ በእሳት ተራምጄ
የጌታ መባልን በጣሙን ናፍቆኛል
ለኔ ሲል የሞተው መቼ ይረሳኛል
ባለም ያለ ምኞት ምንም ላይሟላ
መሸሽ ይጀምራል ሲያልፍ እንደጥላ
ለኔስ በዚህ አለም ያለኝ ተስፋ ምኞት
ከሁሉም በፊት ነው ጌታዬን ለማግኘት
