ፍቅርህ አሸነፈኝ

75

ዛሬ በከፍታ ቦታ አቁመኸኛል
ከጠራሃቸው ጋር አደባልቀኸኛል
በልቤ ታፍኖ የኖረው ፈቅርህ
አሽንፎኝ ወጥቷል ይኸው ላሳይህ

ፍቅርህን አየሁት ወንዙን ሲያሻግረኝ
ፍቅርህን አየሁት ተራራ ሲያወጣኝ
ሁሉንም ችዬ እንዳልፍ ትእግስትን ሲያስተምረኝ

እንደማላውቅ ሁኜ በአጠገብህ ሳልፍ
አልታዘዝ ብዬ ቃልህን ስተላለፍ
ወደ እውነት መንገድ ሲመራኝ አየሁት
ፍቅርህ ነው ደግፎኝ መከራን ያለፍኩት

መውደድ መዋደድን ትርጉሙን ሳላውቀው
ወንድሜን ስጠላ ጉድፉን እያየሁ
ልቤ ዘልቆ ገባ እረቂቁ ፍቅርህ
ትዕቢቴን ሰበረው ተንበረከክሁልህ

እምነቴ ጥልቅ ነው ተራራን ያፈርሳል
ተስፋዬም ብርቱ ነው መንግስት ያወርሰኛል
ብዬ ስመካ ነው እንግዲህ ሁሉ አለኝ
ፍቅር ነው ሚበልጠው ብለህ ያስተማርከኝ

ኢየሱሴ ወዶኛል የእሱም አድርጐኛል
ብዬ እንድመሰክር አንደበቴን ሞልቷል
ከማር የጣፈጠው ፍቅርህ ለማረከኝ
እጆቼን አነሳው አባቴም ባረከኝ

ስለወደድከኝ ነው መፅናኛ የሰጠኸኝ
ማርያም እመቤቴን እናቴ ያደረክልኝ
እንደወደድኋችሁ ተዋደዱ ብለህ
በኔ ውስጥ ታትሞል የማያልቀው ፍቅርህ

እኔስ ኮራሁብህ ሰይጣንም አፈረ
ትቢተኛው ልቤ በፍቅርህ ታሰረ
የታወረው አይኔ ብርሐንን ለየ
ትልቅ ድንቅ ስራህ ዛሬ በኔታየ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top