አዝ. እኔስ አልፈግም ካንተ ሌላ እርካታ /2x/
የኔ ጌታ አሃሃ /4x/ /2x/
1. የነፍሴ ክፍተቷ ሙላቱ አንተነህ
ምንም አይሻትም አንተ በቂዋ ነህ
በህይወት ዘመንዋ ለአንተ እንደተገዛች
በቤትህ ውስጥ ሆና ትዘምራለች
አዝ. ይህ ነው መሻቷ ይህ ነው ፍላጎቷ
የነፍሴ ክበር እየሱሴ
2. ባዶነቷን ይዛ ነፍሴ ወደ አንተ ቀረበች
እንደ ታናሽነቷ መች ባንተ ተናቀች
ዳግም ሣትጠማ ህይወት ካንተ ጠጣችና
ታመሰግናለች ዛሬ ፊትህ ቆማ
አዝ. ተመስገንላት ከፍ በልላት
የኔ ጌታ የነፍሴ እርካታ
3. ለነፍሴ እርካታ ብቸኛው አንተ ነህ
በምንም በማንም ልተካህ የማልችልህ
ለእኔ አንተ በቂ ነህ በህይወት ዘመኔ
ተመስገን ተወደስ እየሱስ መድህኔ
አዝ. ትበቃኛለህ ለኔስ ጌታዬ
ዘለአለም በህይወት ዘመኔ
4. ነፍሴ ሳታቅማማ ተቀብላዋለች
ኢየሱሴ አምላኬ ሁሌም ትለዋለች
ከእርሱ ሌላ አምላክ መቼም አታመልክም
ከእርሱ በላይ እርካታም የትም አታገኝም
አዝ. እርሱ ክብሯ ነዉ እርሱ ጌጥዋ ነው
ለነፍሴ ይክበር አየሱሴ
