የዋልክልኝ ውለታ እጅግ በዛ
ለእኔ ያደረከው ከቁጥር በዛ
ምስጋናን እሰዋልሀሃለሁ
ማዳንህን በአይኔ ስላየሁ
ነውሬን አስወግደህ አየኸኝ በፍቅርህ
አንተ ባትሞትልቃ አልኖርም ነበር
አስበኸኛል ምስኪን ልጅህን
ለካስ ለመልካም ነው ይህ ሁሉ ስራህ /2/
ምስጋና ይገባሃል /4/
ስባዝን በአለም በዝቶ ሃጥያቴ
ነጥቀህ ያወጣኸኝ አንተ ነህ አባቴ
ምላሽ የሚሆነኝ ለዚህ ውለታህ
ምስጋናዬን ላቅርብ ይኸው በቤትህ
አምላኬ ሆይ ምስጋና ይገባሃል
የኛ ኢየሱስ ሞገስ ይገባሃል /2/
የኛ ጌታ ውዳሴ ክብር
የኛ ኢየሱስ ስግደት ይገባሃል
ይድረስህ ምስጋና
አምልኮ
እልልታ
ምስጋና /2/
