እወድሃለሁ

269

ፍቅርህ በዝቶልኝ ጌታ ኢየሱሴ
ላመልክህ መጣሁ ይኸው ከነፍሴ በእወነት ከነፍሴ

እወድሀለሁ /4/ ለዘላለም
ለዘላለም /8/

ለወደድኳት ነፍሴ እንዳንተ አልሆንላት
ላፈቀርኳት ለህይወቴ አልችል ልሞትላት
እጅግ አፍቅረኸኝ ባንተ መጎብኘቴ
ብትወደኝ ነው እንጂ ቀረ መዋተቴ
ቀረ መቃተቴ

ምንስ ኑሮኝ የሚያስወድድ
ምንስ ኑሮኝ የሚያስወድድ
መገኘቴ ባንተ ፊት
መታየቴ ፍቅርህ
መዋጀቴ በደምህ መስዋዕት

እወድሀለሀ /4/ ለዘላለም
እወድሀለሁ /3/ ለዘላለም?
አመልካለሁ /3/ ለዘላለም

አመልክሀለሁ /3/ለዘላለም
አመልክሀለሁ ለዘላለም /4/

ያለምንም ስሌት እንደዚህ ወደድከኝ
ምላሼን ሳትጠብቅ በመስቀል ሞትክልኝ
እንደዚህ ወደኸኝ ባልወድህ ይግረመኝ
ፍቅር ማለት ይኽ ነው ለኔ ያደረክልኝ ለኔ ደም ያፈሰስክልኝ

የደረቀን መንፈስ ሞልተህ ያረሰረስከው
በጎልጎታ መስዋዕት ያኔ ባፈሰስከው
ነፍስህን አሳልፈህ ለኔ የለገስከው
ለምልማ ህይወቴ እባርክሀለሁ እወድስሀለሁ

በትላንት አልበቃህ ዛሬም እየማርከኝ
ሰከኜ እኖራለሁ ነገም ይምጣና እያመለኩኝ
እወድሀለሁ እንደገና
ይበልጥ ልውደድህ ነገም ይምጣና
እወድሀለሁ እንደገና እንደገና
እወድሀለሁ ኢየሱስ እወድሀለሁ

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top