ፍቅርህ መጠጊያዬ ቸርነትህ መታመኛዬ
ቤትህ ማረፊያዬ ምህረትህ መጽናኛዬ
እጅህ ከትከሻዬ ስምህ ምርኩዝ ድጋፌ
እረፍት ጽናት ሰላም
የመውጣት የመግባቴ የመጠበቄ ሰላም
አንተ ነህ በመገኘትህ
የልብ ማረፊያ የነፍሴ ደስታዋ
አንተ ነህ ትሻለኛለህ
የእረኝነትህ ብርታት
ባልፍ እንኳን በሞት ጥላ
ስቃጠል ሆኖኝ ከለላ
ከትከሻዬ በላየ እጆችህን አኖርክና
በረታሁ በድካሜ ላይ
አንተ ትበቃኛለህ ሌላ ሌላ አያሻኝም /2/
ምህረትህ በቤቴ ላይ ሞልቶ ስትጠጋኝ
አቤት ከማለቴ
እንባ ፊቴን ወርሶ በክብርህ ውስጥ ሆኜ
በረከት መሞላቴ
እንደከበበኝ ብርሀን ከመኖርያህም ዙሪያ
አልጠፋም ሁነኝ ጽናቴ
እንዳዲስ ተጠምቼህ አንተን ብቻ ሽቼ
በቃኝ ማየት ጉጉቴን
አቤቱ እንዳንተ ማን ነው ምህረት እውነት የሚወድ /2/
የፈረሰውን ቤቴ ሰርተኸው ማየቴ
ቅጥሬን ጠብቀህ ሆነህ ከፊቴ
የከሳሼን ድምጽ ሽረህ ሆነኸኝ ብርታቴ
ጌታዬ መድሀኒቴ
ከጣራዬ ስር ላላኖር የዲያቢሎስን ድርሻ
ቅራኔ ሚሆን መናኛ
የትናንቱም አልፎ ላልልም ወደ ኋላ
ጸጋህ ከቦኝ ምሳዬም ይሙላ
አቤቱ አንተ ረድተኸኛል አቤቱ አንተ አጽንተኸኛል /2/
