እግዚኣብሔርን አመስግኑት

58

ምህረቱ ለዘላለም ነውና
እግዚአብሔርን አመስግኑት አክብሩት /2/
ቸርነቱ ለዘላለም ነውና
እግዚአብሔርን አመስግኑት አክብሩት /2/

ሰማይን በጥበቡ የሰራ
ምድርን በውሃ ያፀና
ሌሊትን ለፀሐይ ያስገዛው
ፍጥረትን ከጥቂት ያበዛው

አምልኮ በፊቱ ነው
ስግደትም በፊቱ ነው
ለዘላለም የሞላ
ምስጋና በቤቱ አለው

የኛን እልልታ ጭብጨባም
ይደመር እንጨምረው
ይሰማናል እግዚአብሔር
ሁሌም ከእኛ ጋራ ነው

ይምጣ የእጅ መንሻ ይነሳ
ለንጉሱ ክብር ሙገሳ
በህያዋን ዜማ ስንጠራው
እግዚአብሔር ሙሉ ነህ እንበለው

አቤት ምህረት ሲችልበት
አይመረመር በፍጥረት
ጎንበስ ቀና ቢባል ሺ ዓመት
በምን ስሌት ይሄ በዛበት

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top