ኦ ማርያም ሆይ የሰማይ ንግስት
ሰላምን ላኪልን ቅድትስ እመቤት
የአለም ሐጥያት ያልነካሽ
ብፅእት ማርያም አንቺ ነሽ
የልቤን ንፅህና ጠብቂልኝ
ያንቺ መሆኔን አስታውሺኝ
ሕይወታችን አንቺ ነሽ
ደስታችንም አንቺ ነሽ
ተስፋችንም አንቺ ነሽ
ሰላም ላንቺ ይሁን ማርያም
ኦ ቅድስት ማርያም ሆይ
ምስኪኖችን እርጂ
ደካሞችን ደግፊ
የተጨነቁትን አፅናኚ
ስለ ህዝቡ ሁሉ ፀልይ
ስለ ቤተክርስቲያን አስቢ
ስለሃጥያተኞች አማልጂ
ማህበሮቻችንን ጠብቂ
