ሰው አስተውል ረጋ ብለህ
ከንቱ ሩጫህን ገታ አድርገህ
አስቀድመህ ፀድቁን ብትሻው
ይጨመራል ሌላው ሌላው
ስለምድር ብቻ አጥብቀው ቢለፉ
ምንም ውጤት የለው ድካም እንጂ ትርፉ
እጅግ ለሚበልጠው ለሰማዩ እርስትህ
አብዝተህ ብትለፋ ያነው የሚጠቅምህ
የሚያስፈልገንን አስቀሞ ያወቃል
አግ/ር ጨክኖ መች እረስቶህ ያውቃል
ከሌሎች ፍጥረታት ይልቅ አስበልጦ
እግ/ር ያስባል ስለኛ ተገዶ
የሰው አይን ከማየት ፈጽሞ አይጠግብም
ጆሮህም ከመስማት ከቶውንም አይሞላም
የሰው ልጅ ፍላጎት ወሰን የሌለው ነው
የእግ/ር ፅድቅ ግን እርሱ እርካታ ነው
