ከሐጥያቴም አንፃኝ ከብዙ በደሌ
ለዚያች ክፋ ሐጥያት እንዳልሆናት ሎሌ
አንተን ብቻ በደልኩኝ ክፉንም አደረኩኝ
አሁን ይቅር እንደትለኝ ከፊትህ ወደኩኝ
በሐጥያት ታፍኜ እስካሁን ኖሬአለሁ
ጌታዬን ልከተል ይኸው ቆርጫለሁ
ከክፋት አድነኝ እርዳኝ መድሐኒቴ
የነፍሴ አሌታ አንተ ነህ ህይወቴ
የሐጥያቴን ብዛት ቆጥሬ አልዘልቀውም
አምላኬ ሆይ እርዳኝ ሸክሙን አልችለውም
ጌታ እዘንልኝ በጣም ሰድያለሁ
ይቅርታ ልጠይቅ በፊትህ ቆሜያለሁ
አዛኝ ቸር ፈጣሪ አንተ አምላክ ነህና
የይቅርታም አባት ደግሞ የምስጋና
ሲገርፉህ ሲመቱህ ሲበድሉህ ችላህ
ነፃ አወጣኸኝ በመስቀል ተሰቅለህ
እኔንም ለማዳን በመስቀል ላይ ሞተህ
ተጨንቀህ ሞትክልኝ ከዙፋንህ ወርደህ
ፍፁም አለቅህም ከእንግዲህ ጌታዬ
ደስታዬም ምኞቴም አንተነህ አሌንታዬ
