አየሁት

53

ገረመኝ ደነቀኝ የዚህ አለም ነገር
መግለፅም አልቻልኩም ያላብኝን ችግር
ላይ ወጣው ታች ወረድኩ ሁሉንም አየሁት
ሐዘን መከራ እንጂ ደስታንስ አጣሁት

መንገዱ ጠፋብኝ እግሬ ተሳሰረ
ምኞቴም ተስፋዬም ፍፁም ተሰበረ
ከችግር ከአበሳ መትረፌን ሳስበው
በጣም ይገርመኛል እንዴት ልናገረው

እንዲህ ካላ አበሳ መግባቴን ስላየ
በችኮላ መጣ ምንም አልዘገየ
መጨነቄን አይቶ ለቅሶዬን ሲሰማ
ወደ ጠዋት ለወጠው ፍፁሙን ጨለማ

አየሁት ሁሉም ይበቃኛል /2/
አልፈልግም ጌታ ይሻለኛል /2/

የምስጋና መዝሙር ለነፍሴ መድሐኒት
ለኢየሱስ ልዘምር ላዳነኝ ከጥፋት
የድል አክሊል ይሁን ለአንተ መድሐኒቴ
ነፍሴንም ውሰዳት ሁንልኝ አባቴ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top