ከማስተዋል ያለፈ ነው ፍቅርህ
ከመታወቅ ያለፈ ነው ፍቅርህ
ስፋት እርዝመቱ ጥልቀቱ አይገመት
ከአዕምሮ ያልፋል አይወሰንም /2/
ያንተን ፍቅር የሚመዘን አይደለም
በሁኔታ የሚቀየር ባህሪ የለህም
ለኔ ያለህ ፍቅርህ ከቶ አይለወጥም
ዛሬም ትኩስ ነው ፍፁም አይበርድም /2/
ልቤ እርፍ አለ ጌታዬ /2/
ፍቅርህን ቀምሼ
ወደሌላ እንዳልሄድ ወዳጄ /4/
አይቻለሁኝ ጌታ መራራትህን
ከምንም በላይ እኔን መውደድህን /4/
ፍቅርህ እጅግ ግሩም ሆነብኝ
ይሄ መውደድህ ማርኮኝ አስቀረኝ /4/
የሚበልጥ ነገር ከአንተ አገኝቻለሁ
እድለኛ ነኝ በአንተ ተወድጃለሁ /4/ /2/
ልቤ እርፍ አለ ጌታዬ /2/
ፍቅርህን ቀምሼ
ወደሌላ እንዳልሄድ ወዳጄ /4/
