እንዲህ እንዲያ ነው ብዬ

122

እንዲህ ነው እንዲያ ነው ብዬ
ታሪኬን እንዳላወራ እኔማ ምን ታሪክ ኣለኝ
ታሪኬ አንተው ነህና/2/
በመስቀል ስር ሆኗል ታሪኬ ታሪኬ
የሞትክልኝ ለታ አምላኬ አምላኬ
ደምህ የህይወቴ ማተቡ ነውና
የህይወቴ መንገድ ድሉ ነው ዋስትና

ኢየሱስ ሆንክልኝ የኔስ መድሃኒቴ
በአንተ የተነሳ አማረ ህይወቴ
ሌላ ነገር የለም ይሄ ነው ታሪኬ
እድሜዬን በሙሉ የማልፈው ተርኬ

ህይወቴ ጨልሞ ግራ እንደተጋባው
በስጋዬ ኖረ ከህይወት ጠፋው
አንተ ግን ኢየሱስ ህይወቴን ኣዳንከው
በህይወት መዝገብ ላይ ለዘለአለም ፃፍከው

እንዴት ይታለፋል የኔማ ነገር
እጅግ የሚያስደንቅ ግሩም ድንቅ ታምር
በኢየሱስ ሞት ምክንያት ከሞት ተርፌያለሁ
ወግ ደርሶኛል ዛሬ ታሪክ አለ አወራለሁ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top