የጌታን መንገድ አዘጋጁ

243

የጌታን መንገድ አዘጋጁ
ጥርጊያውን ሁሉ አሁን አቅኑ
የጌታ መንግስት ቀርቧልና
ዮሐንስ ይላል እንደገና /2/
የጎበጠው ይቅና ጎድጓዳው ይደልደል

ሁሉም በንስሐ ፊቱ ይቅረብ /2/

መጥረቢያውም ዛፉ ስር ነው
ማይረባውን የሚቆርጠው
መልካም ፍሬ የማያፈራ
በእሳት ይጣላል በተራ

ሁሌም መንሹ በእጁ ነው
ያጠራዋል አውድማውን
በጎተራ ከትቶ ስንዴውን
ያቃጥላል ገለባውን

የጎበጠው ……
የጌታን መንገድ

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top