ክበር ኢየሱስ

71

ክበር /3/ ኢየሱስ አንተ ክበር
ንገስ /3/ ክርስቶስ አንተ ንገስ

በላይ በሰማያት በአብ ቀኝ ያለህ
በመላዕክቶችህም ዙሪያህን ታጅበህ
ንገሥ ለዘለአለም ቅዱስ አንት ብቻ
አልተገኘምና ለአንተ የሚሆንህ አቻ

በሰላም ማደሪያ በመቅደስ ያለህ
ናዝራዊ ኢየሱስ አንተ ሁሌ ትከብራለህ
በምድር ላለነው ትምጣ መንግስትህ
ካንተ ጋራ ሆነን እስቲ እንይ ሞገስህን

ጽኑ መሰረት ነህ የማዕዘን እራስ
ለታመነብህ ሰው ፈጥነህ ህይወት የምታድስ
ክበር በመቅደስህ በዙፋንህ ላይ
ሌላ ማንም የለም ጌታ አንተ ነህ ኤልሻዳይ

ከላይ ከሰማያት ዝቅ ብለህ ወጥተህ
ህዝብህን አዳንከን ጌታ አንተ ተሰቃይተህ
ሞትን ድል ያረከው የአይሁድ አንበሳ
ላንተ ክብር ዛሬም እስቲ እጃችንን እናንሳ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top