ሁሉን ታደርግ ዘንድ አንተ ሁሉን ቻይ ነህ
የሚሳንህ የለም ክቡር ገናና ነህ /4/
ክቡር ገናና ኃይለኛ /5/
ገዥ የሁሉ የበላይ
የለህም ዘላለም የበላይ
አቻ የሚሆንህ በሰማይ
ታሪክ እስቲ ይውጣ ይነገር /2/
ክቡር ……
ስራው ግሩምና ድንቅ ነው
አቤት የኔ ጌታ ልዮ ነው
ማለዳ ማለዳ ምስጋና
ክቡር ……
መከራዬን ከኔ ወሰድከው
ጨለማዬን ደርሰህ ገፈፍከው
ሕይወቴን በብርሃን ሞላህው /2/
ታሪኬን ኢየሱስ ለወጥከው
ክቡር……
በዘላለም ፍቅርህ ወደድከኝ
በከበረው ደምህ ገዛህኝ
አቤቱ ውዴ ሆይ የኔ ነህ /2/
