ይብዛ ምህረትህ

234

ይብዛ ምህረትህ /2/
ጌታ ተመገን
አሜን ተወደስ
ይብዛ ምህረትህ

ደዌ ከፍቶብኝ ልሞት ሳጣጥር
መድሃኒት አጣሁ በሽታ ሚሽር
አለሁህ ያልከኝ ደርሰህ ከጎኔ
ተመስገን የሱስ ቋሚ መድህኔ

አይኖቼን ዳስሶ ብርሃን ያሳየኝ
ገላዬን አይቶ ፈፅሞ አነፃኝ
ተመለክ ጌታ ዛሬም ተወደስ

ክበር እየሱስ ኤልሻዳይ ንጉስ

ጉድፍ ተብዬ የተረሳሁኝ
እንደ ሞተ ሰው የተቆጠርኩኝ
ዛሬ ግን ጌታ ከትቢያ ኣነሳኝ
አለኝታዬ ነው ይባረክለኝ

ሆኜ ቢያየኝ መጥፎ ሐጢያተኛ
ቅን አይታየኝ ላሰው አልተኛ
ተመለስ ልጄ ብሎ ገሰፀኝ
ይመስገን ጌታ ከእሳት አወጣኝ

ምህረት እንደኔ የበዛላችሁ
ስራው ዘወትር ያስደስታችሁ
ተመስገን በሉት አትስጡት ፋታ
ተመስገን ጌታ ሁሌ በእልልታ

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top