ደስ ይበልሽ ደስ ይበልሽ
አንቺ ንፅት ድንግል
ደስ ይበልሽ
ከሴቶቹ ሁሉ የተባረክሽ ነሽ
ሰላም እልሻለሁ ማርያም ድንግል
እንደብስራታዊ እንደገበርኤል
ላንቺ የተሰጠሽ ሁለት ልእልና
አንደኛው በስጋ ሌላው በህሊና
ከአለም ሁሉ ሴቶች ንፅት በመሆንሽ
ሰማያዊ ሚስጥር የተገለጠልሽ
የልኡል ማደሪያ ለመሆን የበቃሽ
የጌታችን እናት በጣም ደስይበልሽ
ማርያም ስትጐበኛት ወደ ቤቷ ገብታ
ኤልሳቤት ዘመረች መንፈስን ተሞልታ
በማሕፀኗ ያለው ዘለለ በደስታ
እኛንም ትጐብኘን ጠዋትና ማታ
