ወዳንተ ነው ጌታ የማየው

140

እንደ አገልጋዮች ዓይኖች
ወደ ጌቶች እጆች

ወዳንተ ነው ጌታ የማየው

እንደ ገረዶች ዓይኖች
ወደ እመቤት እጆች

ወዳንተ ነው ጌታ የማየው

አይኖቻችን ተነስተዋል
ወደ አምላክ አይተዋል

ወዳንተ ነው ጌታ የማየው

በአዛኝነቱ ተመልክቶናል
በፀጋው ምሮናል

ወዳንተ ነው ጌታ የማየው

እረፍቱ አጥለቅልቆናል

ፀጋህ ይበቃናል

ወዳንተ ነው ጌታ የማየው

ትዕቢተኞች ንቀውናል
ሥራችን አዋርዶናል

ወዳንተ ነው ጌታ የማየው

ዘወትር ይሁን ስብሐትም
ላምላካችን ዘላለም

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top