1. ጌታ ፊት ለመቅረብ ለማየት ስንፈራ
ገብርኤልን ጠርተን በርሱ እንመራ
የመሲሁን መምጫ ያወጀው ለዓለም
እርሱን ብንጠራው ያሰጠናል ሰላም
አዝ. ስለዚህ ይመስገን ጠባቂያችን ነው
መልአኩ ገብርኤል ምሥጋና ይግባው
2. የንጉሱንም ሕልም ለዳንኤል አሳየው
ምሥጢሩን ሁሉ አውቆ እንዲተነትነው
ለእኛም ለምስኪኖች የሱስን አሳየን
ከድንግል ተወልዶ ሕዝቦቹን ያዳነን
3. አንተ ባትነግራት ለማርያም ምስጢሩን
ማን ይረዳው ነበር ምሥጢረ ሥጋዌን
ከሁሉም በላይ ነው የተሰጠህ ፀጋ
ያምላክን መወለድ ስታበስረን ለኛ
4. እንደ ቅድስት ማርያም እኛን ሰላም አለን
ካምላክ ጠየቀልን እንድናገኝ ፀጋን
በፍቅር እንድንኖር በመንፈስ ረድቶናል
ወደ ጌታ የሱስ በክንፉ ወስዶናል
