ብዙ ሰጠኸን ጌታ
በተሰጠን እጥፉን ሸለምከኝ
በተሰጠን መልሰህ ባረከን
የደግነትህ ያንተ የፍቅር ለዛ
ዘንግቼው ማየት ተስኖኝ
በዚያው መጠን መስጠት ሲገባኝ
አምቄ ያዝኩት ሌላ እንዳይሻማኝ
ብዙ አደራ አለኝ ጌታ
አደራ ሰጠኸኝ ጌታ
ከተሰጠኝ እንድንሰጥ አዘዝከኝ
ከተሰጠን እንድንሰጥ አዘዝከን
ፈውስን አግኝተን ባንተ በግርማህ ተሞልተን
ሳናደንቅ ምንም እንዳላየን
ብንመለስ በስራህ ተደንቀን
ባረከን ጌታ በምስጋና ልብ ሆነን
ብዙ መገብከን ጌታ
የህይወት እንጀራ ጌታ
አቀረብከን ማዕድ አዘጋጅተህ
ልትመግበን እራስህን ሰውተህ
ስትጋብዘን በሰርግህ አዳራሽ
ልትሰጠን ህይወትን ፈዋሽ
እልል እያልን ቀርበናል ለግብዣ
የማይጠፋን የሰማይ ርስት መያዣ
ቤትህ ሙሉ ነው ጌታ
ብዙ ሀብት ያለህ ጌታ
ስታለብሰኝ የክብርን ሸማ
አደረግክልኝ የነገስታት ጫማ
ልጅህ አድርገህ በቤትህ አክብረህ አኖርከኝ
ሳትነሳኝ ስልጣን እንደሌለኝ
ለታናሹ ፍቅርህን ብትሰጠው
ቀናሁኝ እኔ ፍፁም እንደማላውቀው
