የሚረሳ አይደለም

268

የሚረሳ አይደለም ያንተማ ውለታ
ችዬም አላልፈውም እንዲያው በቸልታ
እስትንፋሴ እስካለ ስላንተ ልዘምር
በጉባኤው መሀል ስራህን ልናገር

ሳልፈራ ልናገር ሳልሰለች ልዘምር /2/
የኔ ጌታ አንተ መልካም ነህ /2/
ኢየሱሴ አንተ መልካም ነህ /2/

ብቆጥረው ብዙ ነው አምላኬ ለእኔ ያደረከው
አይሆንም የዋዛ እንዲሁ በቀላሉ ማልፈው
እስትንፋሴ እስካለ በህይወቴ ሁሌ አዜመዋለሁ
እግዚአብሄር መልካም ነው እያልኩኝ እመሰክራለሁ

ባለፍኩበት ሁሉ በመልካም እጆችህ ደግፈህ
ክፉ እንዳይንካኝ ሁልጊዜ ለእኔ ተጠንቅቀህ
አሳድገኸኛል እንደምን ይረሳል ውለታህ
ለእኔ ደግ አባት ነህ በልቤ እለህ ልዩ ቦታ

ኑሮዬ አማረ ጌትዬ አንተን ያገኘሁ እለት
ምክኒያቱ እንተው ነህ በህይወቴ ዛሬ ላለሁበት
ታዲያ ምን ይገርማል ስላንተ ብዘምር ባወራ
እንዲያው ቢሆንልኝ አንተን ማድነቅ ሁሌ የኔ ስራ

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top