እውነተኛ ሰላም
እንዲወርድልን
ካምላክ አስታርቂን
ማሪያም ማሪያም
ከዙፋንሽ ስር
ወድቀን ተደፍተን
ቅድስት መንበር
እንሳለምሻለን
ሰላምሽ አይለየን
የክርስቶስ እናት
ከልብ አድምጪን
ኦ ንፅእት ኦ ውበት
የለሽ ወደረኛ
ቅድስት ፅጌረዳ
የሰው ልጅ መማፀኛ
ወየው አንቺን ለሚከዳ
በእናትነትሽ
በእንመካበታለን
ለንጹህ ልብሽ
እንሰዋለታለን
ቤተ ክርስቲያን
የተጠማችውን
ሰላም ነፃነትን
ትታደል ከጌታችን
ላንቺ አክብሮት
ልዩ ፍቅር ያለው
የሰማይ እመቤት
እጅግ የታደለ ነው
