የኛ የጌታ /2/ ሞቶ አልቀረም /2/
ሞትን ድል ነስቶ /2/ ሕይወትን ዘራ/2/
መቃብሩ ባዶ ሆኖ ተገኝቷል
ከሙታን መሃል የለም ተነስቷል
ለአለም ሁሉ ምስራች ሆኖአል
ሕያው በመሆን ሞትን ድል ነስቷል
ሐዋሪያቶችም እጅግ ተጨንቀው
በሮችን ዘጉ ጠላትን ፈርተው
ቢያስበረግግም ይህ ጠላታችን
አላማው ከሽፎል በትንሳኤያችን
የተነገረው ሁሉ ሲፈፀም
ድል ኣድራጊያችን ሞቶ አልቀረም
የተገኘው ብርሃን ላለም እንዲያበራ
ዛሬም ትንሳኤን ድልን እናውራ
ሞት ሆይ ድል መንሳትህ ወዴት አለ
የምንልበት የሱስ አስገኘ
ከእንግዲህ ሞትስ ሀይሉ ተነጥቆል
ሕያው የሆነው ሕያው አድርጓል
