ድል ነሳ ጌታ ድልነሳ
ድል ነሳ የሱስ ድልነሳ
ሞትን ረግጦ ተነሳ
እልልታ ለርሱ እልልታ
እልልታ ለርሱ እልልታ
ማህተሙን በሐይሉ ለፈታ
አዝነን ነበር በጣም ተክዘን
ተስፋ ያደረግነው ሞቶ ቢለየን
መመለስ ታክቶን ወደ ቤታችን
በራችንን ዘጋን ኣይሁድን ፈርተን
እየሩሳሌምን ያድናል ያልነው
ሞት አይረታውም ከሞት በላይ ነው 2/
ይዘን ብንመጣ ከርቤና ሽቶ
ጌታን አጣነው የለም ተኝቶ
የተዘጋበት ድንጋዮ እንኳን
ብለን ተናገርን ጌታን ወስደውታል
ኃላ መላእክቱ ሲነግሩን
ሞትን ድል ነስቷል ለካስ ጌታችን 2/
ኤማሁስ ወጣን ተሰቅሎ ልባችን
ስለሱ አወጋን በመንገዳችን
ተቀላቀለን ድንገት መጣና
ድንቅ እስኪለን ጠየቀንና
ማእድ ቀርበን ብላ ብንለው
አይናችን በራ ለካስ ጌታ ነው 2/
ሲነግረን ሳለ ቃላት የለንም
በርግጥ አማኑኤል በህይወት አለ
የምስራች ይዘን መጣንላችሁ
ጌታ ተነስቷል ደስ ይበላችሁ
ሰላም ለናእንተ መጥቶ ያለው
እውነት እየሱስ ሃይለኛ ነው 2/
