የአመታቶች ንጉስ

263

የአመታቶች ንጉስ የዘመናት ጌታ
ሁሉን አሳልፈህ የምትኖር በቦታህ
ክብር ይሁንልህ/2/ የለም የሚመስልህ
ክብር ለቀኖችህ ክብር ለዘመንህ
የለም መሳይ አቻህ

ትላንትም ዛሬም አልፋና ኦሜጋ ፊተኛ ኋለኛ
ትላንትም ዛሬም ለዘላለም ኗሪ የእኛ አምላክ ብቸኛ /2/
ትላንትም ዛሬም በታሪክ ተወስቷል ስንቱ ታሪክ ሆኖ
ትላንትም ዛሬም አንተ ግን አትቆምም ማብቂያ ጊዜህ ደርሶ ይህ አይሆንም ከቶ

ትላንትም ዛሬም የዘላለም እውነት የጊዜ ፈጣሪ
ትላንትም ዛሬም ሁሉን አቀዳጅተህ ቻይ አስተባባሪ ጀማሪ ፈጻሚ
ትላንትም ዛሬም ሁሉን አሳልፈህ አለህ ትኖራለህ
ትላንትም ዛሬም ሁሉን ታደርጋለህ አማካሪ የለህ እግዚአብሔር አንተ ነህ

ትላንትም ዛሬም ዘላለማዊ ነህ ጌታ አንተ በስፍራህ
ትላንትም ዛሬም ሁልጊዜ አዲስ ነው የእለት ተእለት ስራህ ህያው ነህ በስራህ
ትላንትም ዛሬም ዘመናት ሲቆጠር በዘመን ሲተካ
ትላንትም ዛሬም ቀን መቁጠር አይችልም አንተን ግን አይነካም ጌታው ነህ አለቃው

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top