1. ካላገኘሁት ነገር ቀረኝ ከምለው ቁም ነገር
ያረክልኝ ስለበዛ አምላኬ ላመልክህ መጣሁ ከዛ
ከነፍሴ ፈሶ በፊትህ ዙፋንህ ይክበር መቅደስህ
በውስጤ ያለው ይሄ ነው ሁልጊዜ አመሰግንሀለሁ
አመሰግንሀለሁ /8/
2. በጨለማ አለም ቆይቼ እንዳልቀር ልጅህ ጠፍቼ
በኢየሱስ ለእኔ ደርስሀል ህይወቴን ከሞት ታድገሀል
ባንተ ካፈረ ከሳሼ ዝምታ ሳይሆን ምላሼ
በምስጋናዬ መጣሁኝ መች ዝዬ አቋርጣለሁኝ
አመሰግንሀለሁ /8/
3. በህይወት ላኖረኝ ትግስትህ ስለ ዘወትር ጥበቃህ
አቤቱ ስለ ውለታህ ስለማይነገር ስጦታህ
ሳልሳሳ ላብዛ ምስጋና ሌላ የምለው የለምና
አሜን ይድረስህ ውደደው አምላኬ ለክብርህ ስቀኘው
አመሰግንሀለሁ /8/
