ሐረገ ወይን እናታችን
እመቤታችን ሐረገ ወይን
ሐረገ ወይን አንቺ ማርያም ወለተ ሐና ወኢያቄም
ፊደልን እኮ ትመስያለሽ ወንጌልን ትወልጃለሽ መስቀልን ትሰጫለሽ
ማረፊያ ታቦት ትመስያለሽ ጽላትን ትይዣለሽ እመ አምላክ የሚያሰኝሽ
ሐረገ ወይን አንቺ ማርያም
መሶብን ደግሞ ትመስያለሽ ህብስትን ታቀርቢያለሽ ርኀቡን ታጠግቢያለሽ
የምስራቅ ጮራ ትመስያለሽ መብረቅን ታሳያለሽ እርቃኑን ታለብሻለሽ
ሐረገ ወይን አንቺ ማርያም
እናት ሆይ ሰማይ ትመስያለሽ ፀሀይን ታወጫለሽ ብርሃንን ታበርያለሽ
ኣጭቶሻልና ፈጣሪያችን
ይልክ ዘንድ ለዓለም መድህን
ሊያሰጥሽ መንፈሱን
ሐረገ ወይን አንቺ ማርያም
