የክብር ንጉስ

110

የክብር ንጉስ አንተ ነህና
ሺ ዓመት ንገስ ዙፋንህ ይጽና
አቻም የለህ በምድር በሰማይ
ሺ ዓመት ንገስ ሆነህ የበላይ /2/
እግዚአብሔር ይገባሃልና /4/

1. መላዕክት በክብር ያይሃል
ቅዱስ እግዚያብሔር ይሉሀል
መንገስ ይገባሃል ንገሣ
ሁሉም ላንተ ክብር ይነሳ /2/

2. አቻ የለህ እኮ ስትረታ
አቤት ጌታ ያንተስ ችሎታ
ለዘላለም ሹመት ሲያንስ ነው
ንጉስ ሆይ ብትባል ምን ነው /2/

ማነው አንተን እስቲ የመራ
ሰማይን ምድርን ስትሠራ
የሰው ልጅ ታሪኩም ያማረው
ንገስ አግዚያብሔር ባንተ ነው /2/

ላንተ ነው /3/ ክብር የሚገባው
ኦሆ ላንተ ነው ላንተ ነው
ምስጋና የሚገባው ላንተ ነው
ኦሆ ላንተ ነው ላንተ ነው
ክብር የሚገባው ላንተ ነው

ላንተ ነው /3/ ክብር የሚገባው
ክበር እንላለን/2/ በተዋበ ዜማ እናከብርሃለን
ንገስ እንላለን/2/ በእልልታ በሆታ እናደርስሃለ
ከመላዕክቶች ጋር ባንድነት ተስማምተን

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top