የዘለአለም አምላክ የዘለአለም ንጉስ /2/
ቅዱስ ጌታ ኢየሱስ
ዘመን የማይሽረው የነገስታት ንጉስ
አለምን የፈጠርክ የኛ ጌታ ኢየሱስ
ቅዱሳን በሙሉ ስራህን ያወራሉ
ለታላቅነትህ ወድቀው ይሰግዳሉ
በሰማይ በምድር የለም የሚመስልህ
ከአማልእክቶች ሁሉ አንተ ትበልጣለህ
የፍጥረታት ገዢ እግዚያብሔር ድንቅ ነህ
ጌታ ለዘለአለም ፀንትህ ትኖራለህ
ሁሉን የምትችል የሰራዊት ጌታ
በአንተ የታመነ ከቶ ማን ተረታ
የሐያላን ሐያል አቻ የሌለህ ነህ
ለዘለአለም ጌታ ነግሰህ ትኖራለህ
ሐይለኛውን ሁሉ በስልጣን ታዛለህ
የማበሉን ወጀብ ፀጥ ታደርጋለህ
ወጥመድን ሰባብረህ ነፃ ታወጣላህ
ጌታ አምላካችን ይክበርልን ስምህ
