እንዘምርለታለን

61

እንከን የሌለበት የእግዜር በግ የሆነው
የዓለምን ሐጥያት ወስዶ የተሸከመው
ህይወትና እውነት መንገድም ጌታ ነው
ወደርሱ የመጣውን ወደ ውጭ አይጥለው አሜን ወደውጭ አይጥለው

እንዘምርለታለን እንዘምርለታለን /2/
እግዚአብሔር ከፍ ላደረገው ያለገደብ ላከበረው
እንሰግድለታለን እንሰግድለታለን /2/

እስትፋስ ያላችሁ ጌታን አመስግኑ
አቻ አልተገኘለት አምላክ በማዳኑ
አህዛብ ሁላችሁ ጌታን አመስግኑ
አቻ አልተገኘለት እርሱ በማዳኑ /2/
ጌታ በማዳኑ /2/
አምላክ በማዳኑ /2/

የሲኦልንም ሞት መውጊያ የሰበረው
ፍቅሩን በመስቀል ላይ ሞቶ ያስመሰከረው
ራሱን ባዶ አድርጎ ሁሉን ያሸነፈው
የጠፋውን እዳም ኢየሱስ መለሰው አሜን /2/ ኢየሱስ መለሰው

እንዘምርለታለን………….

ከዘመናት በፊት እንደተናገረው
እግዚኣብሔር በልጁ ቃሉን አከበረ
ነፍሱን ሰጥቶ ሰውን ህያው አደረገ
ከሙታን ተነስቶ በክብር አረገ አሜን /2/ በክብር አረገ

መላእክቶች በላይ ይዘምሩለታል
ያለህና የነበርክ ብለው ይጠሩታል
መላእክቶች በላይ ይዘምሩለታል
ቅዱስ ቅዱስ ብለው ፊቱ ይሰግዱለታል / ሁሌ ይሰግዱለታል

እንዘምርለታለን………..

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top