የዘላለም አምላክ

-

የዘላለም አምላክ የዘላለም ንጉስ /2/
ቅዱስ ጌታ ኢየሱስ

1. ዘመን የማይሽረው የነገስታት ንጉስ
አለምን የፈጠርክ የኛ ጌታ ኢየሱስ
ቅዱሳን በሙሉ ስራህን ያወራሉ
ለታላቅነትህ ወድቀው ይሰግዳሉ

የዘላለም አምላክ የዘላለም ንጉስ /2/
ቅዱስ ጌታ ኢየሱስ

2. በሰማይ በምድር የለም የሚመስልህ
ከአማልእክቶች ሁሉ አንተ ትበልጣለህ
የፍጥረታት ገዢ እግዚያብሔር ድንቅ ነህ
ጌታ ለዘለአለም ፀንትህ ትኖራለህ

የዘላለም አምላክ የዘላለም ንጉስ /2/
ቅዱስ ጌታ ኢየሱስ

3. ሁሉን የምትችል የሰራዊት ጌታ
በአንተ የታመነ ከቶ ማን ተረታ
የሐያላን ሐያል አቻ የሌለህ ነህ
ለዘላለም ጌታ ነግሰህ ትኖራለህ

የዘላለም አምላክ የዘላለም ንጉስ /2/
ቅዱስ ጌታ ኢየሱስ

4. ሐይለኛውን ሁሉ በስልጣን ታዛለህ
የማበሉን ወጀብ ፀጥ ታደርጋለህ
ወጥመድን ሰባብረህ ነፃ ታወጣላህ
ጌታ አምላካችን ይክበርልን ስምህ

የዘላለም አምላክ የዘላለም ንጉስ /2/
ቅዱስ ጌታ ኢየሱስ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top